መምረጥ እንዲችሉ ይመዝገቡ
የሚኖሩበትን ስቴት ወይም ግዛት ይምረጡ::
Vote.gov እርስዎን ይረዳዎታል::
ከሰሜን ዳኮታ በስተቀር በሁሉም ስቴቶች ለምርጫ ድምጽ ከመስጠትዎ በፊት መመዝገብ አለብዎት። እርስዎን የሚመለከቱ ህጎች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ወደ ታች ከሚዘረጉ የምርጫ ዝርዝሮች መካከል የሚኖሩበትን ስቴት ወይም ግዛት ይምረጡ ።
የU.S. ዜጎች፥ የU.S. የጦር ሃይል አባላትን እና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ፥ ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ እና የፌደራል ፖስት ካርድ ማመልከቻን (FPCA) በማጠናቀቅ በአካል ሳይገኙ ድምጽ መስጠት ይችላሉ። የU.S. የጦር ሃይል ቤተሰብ አባላት፥ እንደሌላው ማንኛውም ሰው፥ ለመመዝገብ እና የድምጽ መስጫ ለመጠየቅ የU.S.መራጮች የብቃት መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። ለበለጠ መረጃ የፌደራል የመራጮች እርዳታ ሰጪ ፕሮግራምን (በእንግሊዘኛ).
ብሄራዊ የሆነ የመጨረሻ የመራጮች የመመዝገቢያ ቀን የለም። በእያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት ውስጥ ያሉ መራጮች የመራጮች ምዝገባ ሕጎችን መከተል አለባቸው። የመራጮች መመዝገቢያ ቀነ ገደብን ለማግኘት ወደ ታች ከሚዘረጉ የምርጫ ዝርዝሮች መካከል የእርስዎን ስቴት ወይም ግዛት ይምረጡ።
ከሰሜን ዳኮታ በስተቀር የሁሉም ስቴት ዜጎች ለመምረጥ ከፈለጉ እንዲመዘገቡ ይጠይቃሉ። አንዳንድ ስቴቶች መራጮች ከምርጫ 30 ቀናት በፊት እንዲመዘገቡ ይጠይቃሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ እስከ ምርጫ ቀን ድረስ የምርጫ ቀንን ጨምሮ ምዝገባ ይፈቅዳሉ። እርስዎ በሚኖሩበት ስቴት ውስጥ ያሉትን ህጎች ማወቅ ጠቃሚ ነው።
ከሚኖሩበት ስቴት የጊዜ ገደብ በፊት መመዝገብዎን ለማረጋገጥ ወደ ታች ከሚዘረጉ የምርጫ ዝርዝሮች መካከል የሚኖሩበትን ስቴት ወይም ግዛት ይምረጡ። ያ ሊሆን የሚችለው ምርጫው ከመካሄዱ እስከ 30 ቀናት በፊት ነው።
በተጨማሪ ምናልባት ምዝገባዎ “ኢንአክቲቭ” የሚል ምልክት ተደርጎበት እንደሆነ ያረጋግጡ። ቢያንስ በሁለት የፌዴራል ምርጫዎች ካልመረጡ እና የምርጫ ሰራተኞች እርስዎን ለማግኘት ሲሞክሩ ምላሽ ካልሰጡ ምናልባት “ኢንአክቲቭ” ሊሆኑ ይችላሉ።
የኢንአክቲቭ ሁኔታ ማለት እንደገና መመዝገብ ያስፈልግዎታል ማለት አይደለም። ድምጽ ከመስጠትዎ በፊት ተጨማሪ እርምጃዎችን መውሰድ ሊኖርብዎ ይችላል ማለት ነው። የምዝገባ ሁኔታዎን መልሶ ወደ አክቲቭ ለመቀየር ወይም ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የሚኖሩበትን ስቴት የምርጫ ባለስልጣን ቢሮ ወይም የአካባቢዎን ምርጫ ቢሮ ይገናኙ።
በትክክለኛው ስምዎ፣ አድራሻዎ እና የፖለቲካ ፓርቲ ቅርበትዎ መመዝገብዎን ያረጋግጡ። የእርስዎን የመራጭ ምዝገባ መረጃ እንዴት ማስተካከል እንደሚችሉ መረጃ ለማግኘት የሚኖሩበትን ስቴት የምዝገባ ገጽ ይጎብኙ።
የቀየሩት አድራሻ ቅርብም ሆነ ሩቅ፥ አድራሻ ከቀየሩ በኋላ የመራጭ ምዝገባዎን ማስተካከል አለብዎ። በድህረ ገጽ ላይ ወይም በፖስታ እንዴት መመዝገብ እንዳለብዎ ለማወቅ ወደ ታች ከሚዘረጉ የምርጫ ዝርዝሮች መካከል ስቴትዎን ወይም ግዛትዎን ይምረጡ። ምናልባት የእርስዎ ስቴት የመራጮች ምዝገባ በድህረ ገጽ ካለው፥ ያ ለውጦችን ለማድረግ ፈጣኑ መንገድ ሊሆን ይችላል። ከስቴትዎ የምዝገባ ቀነ ገደብ በፊት ለውጦችዎን ያቅርቡ፥ ይህም ከምርጫ ቀን በፊት እስከ 30 ቀናት ሊሆን ይችላል። የእርስዎ ስቴት በተጨማሪ አዲስ መንጃ ፍቃድ ወይም መታወቂያ ካርድ ሊጠይቅዎ ይችል ይሆናል። የእርስዎ ስቴት ምን አይነት የመራጭ መታወቂያ እንደሚጠይቅ ይመልከቱ (በእንግሊዘኛ)።
አድራሻ የቀየሩት ባሉበት ስቴት ውስጥ ከሆነ
አድራሻ የቀየሩት ባሉበት ስቴት ውስጥ ቢሆንም እንኳ፤ ምዝገባዎን በአዲሱ አድራሻዎ ማስተካከል አለብዎ።
አድራሻ የቀየሩት ወደ ሌላ ስቴት ከሆነ
ከአዲሱ ስቴት የምርጫ ምዝገባ ቀነ ገደብ በፊት ይመዝገቡ፤ ይህም ከምርጫው እስከ 30 ቀናት በፊት ድረስ ሊሆን ይችላል። ምናልባት ከምርጫ ቀን በፊት በአዲሱ ስቴትዎ ውስጥ ለመመዝገብ ጊዜ ከሌለዎ፥ የቀድሞ ስቴትዎ በፖስታ ወይም በአካል እንዲመርጡ ሊፈቅድልዎ ይችል ይሆናል። ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሚካሄድባቸው ዓመታት፥ የቀድሞ ስቴትዎ በፖስታ ወይም በአካል እንዲመርጡ መፍቀድ አለበት። ከዚያ በኋላ በአዲሱ ስቴትዎ ውስጥ መመዝገብ ያስፈልግዎታል።
ውጭ አገር ለመኖር መሄድ
ከU.S. ውጭ የሚኖሩ የU.S. ዜጎች የፌደራል ፖስት ካርድ ማመልከቻን (FPCA)(በእንግሊዘኛ)በመሙላት ድምጽ ለመስጠት መመዝገብ እና በአካል ሳይገኙ ድምጽ መስጫ ወረቀት መጠየቅ ይችላሉ። ወታደሮች እና ውጪ አገር ለሚኖሩ ድምጽ አሰጣጥን በሚመለከት ተጨማሪ ግብዓቶችን እንዴት ማግኘት እንደሚችሎ ለማወቅ ይመልከቱ።
እያንዳንዱ ስቴት የፓርቲ ቅርበትዎን ለመምረጥ ወይም ለመቀየር የሚከተለው የተለየ ሂደት አለው። ለመምረጥ በሚመዘገቡበት ወቅት ከየትኛው ፓርቲ ጋር ቅርበት እንዳለዎ ሊጠየቁ ይችሉ ይሆናል፤ ይህም እንደየ ስቴቱ ይለያያል። ያሉበት ስቴት መራጮችን የፖለቲካ ፓርቲ ቅርበት ጥያቄ ላይጠይቅ ይችል ይሆናል። የአሰራር ሂደቱ እንዴት እንደሆነ እና ምናልባት ለሚኖሩበት ቦታ ምን አይነት የጊዜ ገደብ እንዳለ ለማየት የስቴትዎን ወይም የአካባቢዎን ምርጫ ቢሮ ያነጋግሩ። ከፓርቲ ጋር ስላለ ቅርበት ጥያቄ በሁሉም ስቴቶች አይቀርብም።
የመረጡት ፓርቲ ምንም ይሁን ምን፣ በጠቅላላ ምርጫ ጊዜ የምርጫ ሂደቱ አንድ አይነት ነው፤ ይህም እጩዎች ስልጣን እንዲይዙ የሚመረጡበት ግዜ ነው። የእርስዎ ከፓርቲ ጋር ያለዎት ቅርበት በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫዎች እና ካውከሶች (በእንግሊዘኛ) ማንን መምረጥ እንዳለብዎ ተጽእኖ ያሳድራል።
ለመምረጥ ሲመዘገቡ የመራጮች ምዝገባ ካርድ ይላክልዎታል። ይህ ካርድ እንደተመዘገቡ እና ድምጽ ለመስጠት ዝግጁ መሆንዎን ያረጋግጣል። የእርስዎ የመራጭ መመዝገቢያ ካርድ በተለምዶ የእርስዎን ስም፣ የመኖሪያ አድራሻ እና ወደፊት የሚመርጡበትን የምርጫ ጣቢያ አድራሻ ያካትታል። በተጨማሪ የሚኖሩበትን ስቴት የመራጮች ምዝገባ መፈለጊያ ድህረ ገጽ በመጠቀም የትኛው የምርጫ ቦታ እንደተመዘገቡ ማወቅ ይችላሉ።
ምናልባት ስምዎ ወይም አድራሻዎ ከተቀየረ የመራጭ ምዝገባዎን ማስተካከል አለብዎ። አንድ ግዜ የመራጭ ምዝገባ መረጃዎን ካስተካከሉ በኋላ አዲስ የመራጭ ምዝገባ ካርድ ሊላክልዎ ይችል ይሆናል፤ አሰራሩ እንደ ሚኖሩበት ስቴት ይለያያል። ምናልባት ጥያቄዎች ካሉዎት፥ የተሻለ እርዳታ ለማግኘት የአካባቢ የምርጫ ቢሮ ተመራጭ ግብዓት ነው።
ድምጽ ለመስጠት ብዙውን ጊዜ የመራጮች ምዝገባ ካርድ መያዝ የለብዎትም፤ ነገር ግን ሌላ [ለመምረጥ መቅረብ ያለበት የመታወቂያ ዓይነት (በእንግሊዘኛ). ማቅረብ ይኖርብዎ ይሆናል። የበለጠ ለማወቅ የመራጭ ምዝገባ (በእንግሊዘኛ) ይመልከቱ።