ስለ vote.gov

ተልዕኳችን

Vote.gov ከዩኤስ መንግሥት ለአሜሪካ ሕዝብ የሚቀርብ የታመነ እና ትክክለኛ ይፋዊ የምርጫ መረጃ ምንጭ ነው። ተልኳችን ሁሉም ለመምረጥ ብቁ የሆኑ መራጮች እንዴት መመዝገብ እና መምረጥ እንደሚችሉ በቀላሉ እንዲገነዘቡ ማድረግ ነው፡፡

Vote.govስቴት ተኮር የሆኑ የምርጫ መረጃዎችን እንዲያገኙ መራጮችን ወደ የሚኖሩበት ስቴት ድረ ገጾች ይመራል፡፡ Vote.gov ሰዎችን እንዲመርጡ ለማድረግ አይመዘግብም፡፡ እርስዎ በሚገኙበት ስቴት በቀጥታ መመዝገብ አለብዎት፡፡ Vote.gov ከሕዝቡ ማናቸውንም ግላዊ መረጃዎች ባለመሰብሰብም ሆነ ባለማስቀመጥ ለተጠቃሚዎች ግላዊነት ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

Vote.gov የምርጫ መረጃዎችን በበርካታ ቋንቋዎች ያቀርባል፡፡ የU.S. Census Bureau ወደ 70 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ በቤት ውስጥ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ሌላ ቋንቋ እንደሚናገሩ ሪፖርት አድርጓል፡፡ የዩኤስ. ዜጎችን ብዝሃነት በሚያንጸባርቅ መልኩ የምርጫ መረጃዎችን በልዩ ልዩ ቋንቋዎች በማቅረብ ሰዎች የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙ እናደርጋለን፡፡ 

ስለ ማንነታችን

Vote.gov በGeneral Services Administration ስር በTechnology Transformation Services (በእንግሊዘኛ) የሚመራ የዩኤስ መንግሥት ይፋዊ ድረ ገጽ ነው፡፡

እምነት የሚጣልበትን እና ወጥነት ያለው የምርጫ መረጃ ማቅረባችንን ለማረጋገጥ ከU.S. Election Assistance Commission (በእንግሊዘኛ) እንዲሁም ከCybersecurity and Infrastructure Security Agency (በእንግሊዘኛ) ጋር በአጋርነት እንሰራለን፡፡

በተጨማሪም ከሌሎች የፌዴራል መንግሥት ኤጀንሲዎች ማለትም ከFederal Voting Assistance Program፣ ከU.S. Citizenship and Immigration Services እና ከDepartment of Stateን ጨምሮ አብረን በመሥራት ሰዎች ከሌሎች የመንግሥት አገልገሎቶች ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር ስለምርጫ መረጃ እንለዋወጣለን፡፡

ትክክለኛ የስቴት የመራጮች መረጃ መለዋወጣችንን ለማረጋገጥ ከስቴት እና ከአካባቢ የምርጫ ባለስልጣናት ጋር በNational Association of Secretaries of State እና በNational Association of State Election Directors በኩል ቅርብ የሆነ ግንኙነት አለን።

 

ይመዝገቡ