ለመመዝገብ የምዝገባ አማራጮች አሉዎት
እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት ለምርጫ ለመመዝገብ የራሱን ደንብ ያወጣል፡፡ ከዚህ የሚከተሉትን ማድረግ ይችሉ ይሆናል፦
ምዝገባዎ የዘመነ መሆኑን ያረጋግጡ
በስቴትዎ ድረገጽ በትክክለኛው ሕጋዊ ስምዎ እና አድራሻዎ መመዝገብዎን ያረጋግጡ፡፡ በበርካታ ስቴቶች በተጨማሪ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫዎች እርስዎ በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመዘገቡ ሊጠይቁ ይችላሉ። የመራጭ ምዝገባ ሁኔታዎን ለማረጋገጥ በስቴትዎ የምርጫ ድረገጽ ላይ ስቴትዎን ወይም ግዛትዎን ይምረጡ፡፡
በመጨረሻዎቹ ሁለት የፌዴራል ምርጫዎች ድምጽ ካልሰጡ ወይም የምርጫ ኃላፊዎች ሊያገኙዎ ሲሞክሩ ካልተገኙ ምዝገባዎ “ንቁ ያልሆነ” ተብሎ ሊያዝ ይላል፡፡ የስቴትዎ ወይም የአካባቢዎ የምርጫ መሥሪያ ቤት ምዝገባዎን ወደ ንቁ ለመቀየር ሊያግዝዎ ወይም ጥያቄ ካለዎ መልስ ሊሰጥዎ ይችላል፡፡
በመራጭ ምዝገባዎ ላይ አድራሻዎን ይቀይሩ
ከአድራሻ ለውጥ በኋላ በስቴት ውስጥም ሆነ ከስቴት ውጪ የተዘዋወሩ እንደሆነ የመራጭ ምዝገባዎን ወቅታዊ ማድረግ ያስፈልግዎታል፡፡ ምናልባት ከስቴት ውጪ ከተዘዋወሩ፤ ለመኖር በሄዱበት ስቴት ይመዝገቡ፡፡ የእርስዎ ስቴት ምዝገባ መጨረሻ ቀን ከመድረሱ በፊት ለውጦቹን ያሳውቁ፤ ይህም የምርጫ ቀን ከመድረሱ ከ30 ቀናት አስቀድሞ ሊሆን ይችላል፡፡
ምናልባት የምዝገባ ቀን በማለፉ ምክንያት ከፕሬዚደንታዊ አጠቃላይ ምርጫ በፊት በአዲሱ ስቴትዎ ለመመዘገብ ጊዜ ከሌለዎ፤ የቀድሞው ስቴት በፖስታ ወይም በአካል እንዲመርጡ መፍቀድ አለበት፡፡ ከፕሬዚደንታዊ ምርጫ ውጪ የእርስዎ ስቴት እንዲመርጡ ሊፈቅድልዎ ይችላል፡፡ ከዚያ በኋላ በአዲሱ ስቴትዎ መመዝገብ አለብዎ፡፡
መረጃዎን ወቅታዊ ለማድረግ የሚኖሩበትን ስቴት ወይም ግዛት ይምረጡ፡፡
በመራጭ ምዝገባዎ ላይ ስምዎን ይቀይሩ
ሕጋዊ ስምዎን ከቀየሩ በኋላ በስቴትዎ ወይም በግዛትዎ የመራጭነት ምዝገባዎን ማዘመን አለብዎ፡፡ መረጃዎን ለማዘመን ስቴትዎን ወይም ግዛትዎን ይምረጡ፡፡
ከስቴትዎ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን በፊት ለውጦችዎን ያቅርቡ፡፡ ለአካባቢ፣ ለስቴት ወይም ለብሔራዊ ምርጫ የስቴትዎ የምዝገባ የመጨረሻ ቀን ከምርጫ ቀን ከ30 ቀናት አስቀድሞ ሊሆን ይችላል፡፡ በሚመዘገቡበት ጊዜ ስቴትዎ በተጨማሪ ወቅታዊ የመንጃ ፈቃድ ወይም መታወቂያ እንዲያቀርቡ ሊጠይቅዎ ይችላል፡፡
የሚደግፉትን ፓርቲ ይቀይሩ
ድምጸ ለመስጠት በሚመዘገቡ ጊዜ፤ አንዳንድ ስቴቶች እና ግዛቶች ስለፓርቲ ድጋፍዎ ሊጠይቁዎ ይችላሉ፡፡ ዝግ የመጀመሪያ ደረጃ ምርጫ (በእንግሊዘኛ) ስቴቶ እና ግዛቶች መምረጥ የሚችሉት በመጀመሪያ ደረጃ የፓርቲዎ ምርጫ ብቻ ነው፡፡ በጠቅላላ ምርጫዎች የፓርቲ ምርጫዎ የትኛውም ቢሆን ለማንኛውም እጩ ድምጽዎን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
የፓርቲ ምርጫዎን እንዴት ማዘመን እንደሚችሉ ለማወቅ ስቴትዎን ወይም ግዛትዎን ይምረጡ፡፡ ስቴትዎ በአዲሱ የፓርቲ ምርጫዎ መሠረት በድጋሚ እንዲመዘገቡ እና ቅጽ እንዲሞሉ ሊጠይቁዎ ወይም በአካባቢ የምርጫ መሥሪያ ቤት ተገኝተው የፓርቲ ምርጫዎን ለመቀየር አማራጮች ሊሰጠዎ ይችላሉ፡፡
የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን ይወቁ
በብሔራዊ ምርጫ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን የለም፡፡ በአንዳንድ ስቴቶች የመጨረሻው የምዝገባ ቀን ከምርጫው ቀን ከ30 ቀናት አስቀድሞ ነው፡፡ በሌሎች ስቴቶች ደግሞ በምርጫ ቀን መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ቀን የሚለው አገላለጽ ማንኛውንም ምርጫ የሚመለከት ነው (የአካባቢ፣ የስቴት ወይም ብሔራዊ ምርጫ)። በስቴትዎ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀንን ያግኙ (በእንግሊዘኛ)፡፡
የመራጭ ምዝገባ ካርድዎ
ለመምረጥ ሲመዘገቡ ወይም ምዝገባዎን ሲቀይሩ፤ የመራጭ የምዝገባ ካርድ ይላክልዎታል፡፡ ይህ ካርድ ለመምረጥ መመዝገብዎን እና ዝግጁ መሆንዎን ያረጋግጣል፡፡ ለመምረጥ የመራጭ ምዝገባ ካርድዎን መያዝ አይጠበቅብዎትም፤ ነገር ግን አንዳች ዓይነት ማንነትዎን ለመለየት የሚያስችል መታወቂያ ማቅረብ ይኖርብዎት ይሆናል፡፡ በስቴት ወይም በአካባቢ ምርጫ ድረገጽ (በእንግሊዘኛ) የመራጭ ምዝገባ ካርድ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ይወቁ፡፡
ከዩኤስ ውጭ ነዋሪ ሆነው ሳለ ስለመምረጥ
የU.S. ዜጋ ከሆኑ እና ከU.S. ውጪ ነዋሪ ከሆኑ፣ Federal Post Card Application (በእንግሊዘኛ) በመሙላት ለመምረጥ መመዝገብ እና የቀሪ (ፖስታ) ድምጽ መስጫ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የU.S. የጦር ሠራዊት አባል ከሆኑ ወይም የጦር ሠራዊት አባል ቤተሰብ ካለዎት ድምጽ ለመስጠት የFederal Post Card Application መሙላት እና የቀሪ ድምጽ መስጫ እንዲሰጥዎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የጦር ሠራዊት አባላት እና በውጭ አገር ያሉ መራጮች ከFederal Voting Assistance Program (በእንግሊዘኛ) ተጨማሪ መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡