እንደ ኮሌጅ ተማሪ ስለመምረጥ

መምረጥ ማኅበረሰባችሁን ለማቅናት ሃይል ይሰጥዎታል፡፡

Female student at a voting booth

የመራጭነት ምዝገባዎ ከመኖሪያ ቦታዎ ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ እንደ ኮሌጅ ተማሪ እርስዎ በሚኖሩበት ስቴት የመኖሪያ መስፈርቶች ላይ ተመስርቶ በአብዛኛው በመኖሪያ አካባቢዎ ወይም የኮሌጅ ትምህርት በሚማሩበት ስፍራ መመዝገብ ይችላሉ፡፡ አስታውሱ፦ ከአንድ በላይ በተለያዩ ቦታዎች ሊኖሩ ይችላሉ ነገር ግን ለመምረጥ የሚችሉት በአንድ ቦታ ላይ ብቻ ነው፡፡

ከመኖሪያ ከተማዎ እና ከኮሌጅ ከተማዎ አንዱን ምረጡ

ምናልባት የኮሌጅ ትምህርት የሚማሩት ከመኖሪያ ከተማዎ ውጪ በሌላ ከተማ ከሆነ፣ የት እንደሚመርጡ ለመወሰን ከግምት ሊያስገቧቸው ከሚችሏቸው ነገሮች መካከል የተወሰኑት ከዚህ በማስከተል ይገኛሉ፦ 

  • ለእርስዎ ይበልጥ የሚያመቸው የትኛው ቦታ ነው? 
  • በእያንዳንዱ ቦታ ለምርጫ የቀረበው ማነው?
  • ከሁለቱ ቦታዎች በአንዳቸው ለእርስዎ ጠቃሚ የሆኑ የአካባቢ ፖሊሲዎች ወይም ዓይነተኛ ጉዳዮች አሉ ወይ?

ለመምረጥ የሚመዘገቡበት ስፍራ በፌዴራል የገንዘብ ድጋፍ ላይ ተጽዕኖ አይኖረውም፤ ከእነርሱም መካከል Free Application for Federal Student Aid፣ Pell Grants፣ Perkins ወይም Stafford loans ይገኙባቸዋል፡፡ ይህም በስቴት ውስጥ ለሚኖሩ ተማሪዎች የትምህርት ክፍያ ብቁ በመሆንዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል ይሆናል፡፡

በመኖሪያ ከተማዎ ስለመምረጥ

ምንም እንኳ ከዓመቱ ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ከመኖሪያ ከተማዎ ርቀው ትምህርት ቤት ቢሆኑም በመኖሪያ ከተማዎ የመምረጥ አማራጭ ይኖርዎታል፡፡ ማስታወስ ያለብዎ ከዚህ የሚከተለው ነው፦

  • በመኖሪያ ከተማዎ ያለውን ቋሚ አድራሻዎን በመጠቀም ለመምረጥ ይመዝገቡ፡፡ በምዝገባው ላይ የኮሌጁን አድራሻ እንደ ፖስታ አድራሻ አድርገው ይጠቀሙ፡፡
  • በብዙዎች ስቴቶች በአካል ተገኝተው መምረጥ የማይችሉ ከሆነ የፖስታ ድምጽ መስጫ እንዲጠይቁ ይፈቅዳሉ፡፡ አንዳንድ ስቴቶች ለእያንዳንዱ መራጭ ድምጽ መስጫ ወረቀቶችን ወዲያውኑ ይልካሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰቴት የራሱ የሆነ መመሪያ አለው፣ ስለሆነም በእርስዎ ስቴት ወይም ግዛት ደንቦቹ ምን እንደሆኑ ለማወቅ አረጋግጡ (በእንግሊዘኛ)። የፖስታ ድምጽ መስጫዎን ወደ ኮሌጅዎ አድራሻ እንዲላክልዎ ሊያደርጉ ይችላሉ። 
  • ምናልባት በምርጫው ጊዜ በመኖሪያ ከተማዎ የምትገኙ ከሆነ፣ በተጨማሪ በአካል የመምረጥ አማራጭ ሊኖርዎት ይችላል፡፡ በምርጫ ቀን ወይም ከምርጫ ቀን በፊት የት እንደምትመርጡ ለማወቅ የምርጫ ቦታ አመልካች (በእንግሊዘኛ) ይቀሙ፡፡ 

በመኖሪያ ስቴትዎ ውስጥ በሌላ ከተማ ስለመምረጥ

ምናልባት በመኖሪያ ስቴትዎ ወይም ግዛትዎ የኮሌጅ ትምህርት የሚከታተሉ ከሆነ፤ በዚያ ለመምረጥ አማራጭ ሊኖርዎ ይችላል፡፡ ማስታወስ ያለብዎ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦

  • ምናልባት ለመምረጥ የተመዘገቡት ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ፤ ስቴትዎ ለመምረጥ የነዋሪነት መስፈርቶች ምን እንደሆኑ አረጋግጡ፡፡ በዚያ ስፍራ ለመራጭነት ለመመዝገብ ለተወሰኑ ቀናት ጊዜ በዚያ ስፍራ መኖር ሊጠበቅብዎ ይችል ይሆናል፡፡
  • ብቁ መሆንዎን ካረጋገጡ በኋላ፣ በካምፓሱ ውስጥ ወይም ውጪ የምትኖረበትን ሕንጻ አድራሻ በመጠቀም ሊመዘገቡ ይችላሉ። ለመመዝገብ የካምፓስ የፖስታ ሳጥን አይጠቀሙ፤ ነገር ግን የካምፓሱን የፖስታ አድራሻ መላኪያ የፖስታ አድራሻ አድርገው ሊጠቀሙ ይችላሉ። ምናልባት የትኛውን አድራሻ እንደሚጠቀሙ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ የትምህርት ቤትዎን የሲቪክ ተሳትፎ ጽ/ቤት ወይም የምርጫውን ጽ/ቤት ይጠይቁ፡፡ 
  • ምናልባት በመኖሪያ ከተማዎ ለመምረጥ ተመዝግበው ከሆነ፤ የመራጭነት ምዝገባዎን ለማዘመን የኮሌጅዎን አድራሻ ይጠቀሙ፡፡ የትኛውን አድራሻ እንደሚጠቀሙ ተጨማሪ ምሪት ለማግኘት፤ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት አነጋግሩ (በእንግሊዘኛ)፡፡
  • ምናልባት አስቀድሞ ምርጫ ሲደረግ ወይም በምርጫ ቀን ወደ መኖሪያ አካባቢዎ መሄድ የሚችሉ ከሆነ፤ ምርጫው የሚካሄድበትን ስፍራ ለማወቅ የምርጫ ቦታ ጠቋሚ (በእንግሊዘኛ) ተጠቀሙ፡፡
  • አንዳንድ ስቴቶች በአካል ተገኝተው ለመምረጥ ካልቻሉ ወይም በፖስታ መምረጥን ከመረጡ የቀሪ ወይም የፖስታ ድምጽ መስጫ እንዲጠቀሙ ይፈቅዳሉ፡፡ አንዳንድ ስቴቶች ሙሉ በሙሉ በፖስታ ምርጫዎች ያካሂዳሉ፡፡ እያንዳንዱ ስቴት የየራሱ መምሪያ ያለው በመሆኑ የስቴቱን ወይም የግዛቱን ደንቦች አረጋግጡ፡፡

ከስቴቱ ውጪ በኮሌጅ ከተማዎ ስለመምረጥ

ምናልባት የኮሌጅ ትምህርት የሚከታተሉት ከመኖሪያ ስቴትዎ ውጪ በሚሆን ጊዜ በዚያ የመምረጥ አማራጭ አለዎ፡፡ ማስታወስ ያለባችሁ ከዚህ የሚከተለው ነው፦

  • በአንዳንድ ስቴቶች በዚያ ለምርጫ ለመመዝገብ በስቴቱ የተወሰኑ ቀናት መኖር አለባችሁ፡፡ ኮሌጃችሁ በሚገኝበት ስቴት የምርጫ መሥሪያ ቤት ድረገጽ (በእንግሊዘኛ) የነዋሪነት መስፈርቶችን አረጋግጡ፡፡ 
  • ብቁነታችሁን ካረጋገጡ በኋላ፤ ኮሌጅዎ በሚገኝበት ስቴት ለመምረጥ ይመዝገቡ፡፡ ለመምረጥ በካምፓስ ወይም ከካምፓስ ወጪ የምትኖሩበትን ሕንጻ አድራሻ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ለመመዝገብ የካምፓስ የፖስታ ሳጥን አይጠቀሙ፤ ነገር ግን የካምፓሱን የፖስታ ሳጠን እንደ መላኪያ አድራሻ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡ ምናልባት የትኛውን አድራሻ እንደሚጠቀሙ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ የትምህርት ቤትዎን የሲቪክ ተሳትፎ ጽ/ቤት ወይም የምርጫውን ጽ/ቤት ይጠቀሙ፡፡ 
  • በመኖሪያ ስቴትዎ ለመምረጥ ተመዝግበው ነገር ግን ምዝገባዎንኮሌጁ ወደሚገኝበት ስቴት ለመቀየር ይፈልጋሉ? አብዛኞቹ ካውንቲዎች እና ስቴቶች ወደ ሌላ ስፍራ ስትዘዋወሩ የመራጭነት ምዝገባችሁን እንድትሰርዙ ይጠይቃሉ። ነገር ግን ብዙዎች የስቴት እና የአካባቢ መሥሪያ ቤቶች ምዝገባችሁን ለመሰረዝ ልትጠቀሙበት የምትችሉት ቅጽ አላቸው፡፡ የመራጭ ስረዛ ቅጾች ለማግኘትየስቴት ወይም የአካባቢ ምርጫ መሥሪያ ቤቱን አግኙ (በእንግሊዘኛ)፡፡

በውጭ አገር በትምህርት ላይ እያሉ ስለመምረጥ

ምናልባት የዩኤስ ዜጋ ከሆኑ በዓለም ውስጥ በማንኛውም ስፍራ ሆነው ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ ከዩኤስ ውጪ ሆነው ስለመምረጥ በይበልጥ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡ 

ለመምረጥ ስለመመዝገብ

አንድ ግዜ ከተመዘገቡ በኋላ ዓመቱን በሙሉ በአካባቢ፣ በስቴት እና በፌዴራል ምርጫዎች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ 

ለመመዝገብ የምዝገባ አማራጮች አሉዎት

እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት ለምርጫ ለመመዝገብ የራሱን ደንብ ያወጣል፡፡ ከዚህ የሚከተሉትን ማድረግ ይችሉ ይሆናል፦ 

የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን ይወቁ

በብሔራዊ ምርጫ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን የለም፡፡ በአንዳንድ ስቴቶች የመጨረሻው የምዝገባ ቀን ከምርጫው ቀን ከ30 ቀናት አስቀድሞ ነው፡፡ በሌሎች ስቴቶች ደግሞ በምርጫ ቀን መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ቀን የሚለው አገላለጽ ማንኛውንም ምርጫ የሚመለከት ነው (የአካባቢ፣ የስቴት ወይም ብሔራዊ ምርጫ)። በስቴትዎ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀንን ያግኙ (በእንግሊዘኛ)፡፡ 

ለመምረጥ ዝግጁ ነዎት?

በምርጫ ለመሳተፍ እንዲችሉ ከእርስዎ የጊዜ ሰሌዳ አንጻር ምቹ እንዲሆን እና ግላዊ ፍላጎቶችዎን እንዲያሟላ የሚያስችሉ አማራጮች አሉ፡፡

የመራጮች መለያ መስፈርቶች

እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት የየራሱን የመራጭ መለያ ደንቦች ያወጣል፡፡ በአብዛኛዎቹ ስቴቶች በአካል ተገኝተው መምረጥ መታወቂያዎን ይዘው መቅረብ፤ በፖስታ አማካኝነት ሲመርጡ ደግሞ የማንነትዎን መረጃ መስጠት አለብዎ፡፡ የስቴትዎን የመራጭ መታዊቂያዎች መስፈርቶችን ያረጋግጡ (በእንግሊዘኛ)፡፡

ምንም እንኳን የማያሽከረክሩ ቢሆንም ከስቴትዎ የሞተር ተሽከርካሪ መሥሪያ ቤት መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ፡፡ መታወቂያ ለማግኘት ክፍያ መፈጸም ይኖርብዎታል፤ ነገር ግን ከመታወቂያ ጋር ለተያያዙ ክፍያዎች ምናልባት እገዛ ሊያደርጉልዎ የሚችሉ ድርጅቶች አሉ፡፡

ድምጽ ለመስጠት የመራጭ መለያ ካርድ አያስፈልገዎትም፡፡

ስለድምጽ መስጫዎ ይወቁ

የሚሰጡት ድምጽ በማኅበረሰቡ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በማወቅ መረጃ እንዳገኘ ሰው እንዴት መምረጥ እንዳለብዎ ይማሩ፡፡

በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ናሙና ድምጽ መስጫዎችን በኢንተርኔት ላይ ይለጥፋሉ፡፡ አንዳንዶች እንዲሁ በኢንተርኔት አማካኝነት ወይም በፖስታ ስለ እጩዎች እና ስለ ድምጽ እርምጃዎች መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የስቴትዎን ወይም የአካባቢዎን የምርጫ ዌብሳይት ይፈትሹ፡፡

የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን ይመዝገቡ

ክፍያ የሚከፈለው የምርጫ ሠራተኛ በመሆን ማኅበረሰብዎን ይደግፉ፡፡ የምርጫ ሠራተኛ ተግባራት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ ተመስርቶ የተለያዩ ናቸው፡፡ በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ሥራዎችን የሚሰሩ የምርጫ ሠራተኞች አሏቸው፣ ከሥራዎቹም መካከል፦

  • የምርጫ ቦታ ማዘጋጀት 
  • መራጮችን መቀበል 
  • የመራጭ ምዝባን ማረጋገጥ 
  • ድምጽ መስጫን ማሰራጨት  
  • መራጮች የመምረጫ መሣሪያዎች እንዲጠቀሙ ማገዝ 
  • የምርጫ አካሄድን ማብራራት 

እንደ ምርጫ ሠራተኛ ለጊዜዎ ክፍያ ያገኛሉ፡፡ የክፍያው መጠን በቦታው ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እንዴት የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን እንደሚችሉ በይበልጥ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡