መምረጥ የወደፊት ሕይወትዎን ለማስተካከል እና በማኅበረሰብዎ ውስጥ ንቁ አባል እንዲሆኑ ሃይል ይሰጥዎታል፡፡
በምርጫ ጉዞዎ የመጀመሪያውን እርምጃ ይራመዱ - ይመዝግቡ
በአብዛኞቹ ስቴቶች፣ በDistrict of Columbia እና በU.S.ግዛቶች የ18 ዓመት ዕድሜ ሳይሞላዎ በፊት ቅድመ ምዝገባ ማድረግ (በእንግሊዘኛ) ይችላሉ፤ ነገር ግን ለመምረጥ የ18 ዓመት ዕድሜ የሞላዎት መሆን አለበት፡፡ በርአካታ ስቴቶች በጠቅላላ ምርጫ ጊዜ 18 ዓመት የሚሞላዎ ከሆነ በ17 ዓመት እድሜዎ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫዎች እንዲሳተፉ ይፈቅዳሉ፡፡ ስለ ስቴትዎ ደንቦች ይበልጥ ይወቁ (በእንግሊዘኛ) እና ወደፊት ስለሚኖር የአካባቢዎ የምርጫ ቀናት ይወቁ በስቴቱ የምርጫ ድረገጽ (በእንግሊዘኛ)።
ዝግጁ እንዲሆኑ የምርጫ ዕቅድ ያውጡ
የምርጫ ዘዴዎች እንደየስቴቱ እና ግዛቱ የተለያዩ ናቸው። አብዛኞቹ ስቴቶች ለመምረጥ መመዝገብ እና ምርጫ ከእርስዎ የጊዜ ሰሌዳ እና ግላዊ ፍላጎት አንጻር የተመቻቸ እንዲሆን ተለዋዋጭ አማራጮችን ያቀርባሉ፡፡
ለመመዝገብ የምዝገባ አማራጮች አሉዎት
እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት ለምርጫ ለመመዝገብ የራሱን ደንብ ያወጣል፡፡ ከዚህ የሚከተሉትን ማድረግ ይችሉ ይሆናል፦
- ኦንላይን ላይ ይመዝገቡ፦ ብዙዎች ስቴቶች በኦንላይን እንዲመዘገቡ ይጋብዛሉ፡፡ ምናልባት በኦንላይን መመዝገብ ይችሉ እንደሆነ ለማወቅ ስቴትዎን ወይም ግዛትዎን ይምረጡ፡፡
- በፖስታ ለመምረጥ ስለመመዝገብ፦ ከNew Hampshire, North Dakota, Wisconsin እና Wyoming ውጪ በእያንዳንዱ ስቴት ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ብሔራዊ በደብዳቤ ምርጫ ምዝገባ ቅጽ (በእንግሊዘኛ) ማውረድ እና ማተም ይችላሉ፡፡ ቅጹ በበርካታ ቋንቋዎች ይገኛል፡፡
- በአካል ስለመመዝገብ፦ በበስቴት ወይም በአካባቢዎ የምርጫ መሥሪያ ቤት (በእንግሊዘኛ) ወይም በስቴትዎ የሞተር ተሽከርካሪ መሥሪያ ቤት ሊመዘገቡ ይችላሉ፡፡
የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን ይወቁ
በብሔራዊ ምርጫ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን የለም፡፡ በአንዳንድ ስቴቶች የመጨረሻው የምዝገባ ቀን ከምርጫው ቀን ከ30 ቀናት አስቀድሞ ነው፡፡ በሌሎች ስቴቶች ደግሞ በምርጫ ቀን መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ቀን የሚለው አገላለጽ ማንኛውንም ምርጫ የሚመለከት ነው (የአካባቢ፣ የስቴት ወይም ብሔራዊ ምርጫ)። በስቴትዎ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀንን ያግኙ (በእንግሊዘኛ)፡፡
የመራጮች መለያ መስፈርቶች
እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት የየራሱን የመራጭ መለያ ደንቦች ያወጣል፡፡ በአብዛኛዎቹ ስቴቶች በአካል ተገኝተው መምረጥ መታወቂያዎን ይዘው መቅረብ፤ በፖስታ አማካኝነት ሲመርጡ ደግሞ የማንነትዎን መረጃ መስጠት አለብዎ፡፡ የስቴትዎን የመራጭ መታዊቂያዎች መስፈርቶችን ያረጋግጡ (በእንግሊዘኛ)፡፡
ምንም እንኳን የማያሽከረክሩ ቢሆንም ከስቴትዎ የሞተር ተሽከርካሪ መሥሪያ ቤት መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ፡፡ መታወቂያ ለማግኘት ክፍያ መፈጸም ይኖርብዎታል፤ ነገር ግን ከመታወቂያ ጋር ለተያያዙ ክፍያዎች ምናልባት እገዛ ሊያደርጉልዎ የሚችሉ ድርጅቶች አሉ፡፡
ድምጽ ለመስጠት የመራጭ መለያ ካርድ አያስፈልገዎትም፡፡
በአካል ስለመምረጥ
ብዙዎቹ በምርጫ ቀን የሚመርጡ ሰዎች በምርጫው ቦታ በአካል ተገኝተው መምረጥ አለባቸው፡፡ በምርጫ ቦታው ላይ ሲደርሱ፣ የምርጫ ሠራተኞች እርስዎን ለማገዝ ዝግጁ ሆነው ያገኟቸዋል፡፡ በወረቀት ድምጽ መስጫ አማካኝነት የሚፈልጓቸውን በመምረጥ ወይም የኤሌከትሮኒክ መሣሪያ በመጠቀም ድምጽ ይሰጣሉ፡፡
የእርስዎን የምርጫ ቦታ ያግኙ (በእንግሊዘኛ)። የምርጫ ቦታ መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜያት ከአካባቢ አካባቢ የስልጣን ሽፋን መሰረት ይለያያሉ፡፡ ምናልባት ስለምርጫ ቦታዎ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት የስቴት ወይም የአካባቢ የምርጫ መሥሪያ ቤቶችን (በእንግሊዘኛ) ያነጋግሩ፡፡
ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት
አንዳንድ የድምጽ መስጫ ቦታዎች ከምርጫ ቀን በፊት ክፍት ናቸው፡፡ በስቴትዎ ወይም ግዛትዎ ቀደም ብሎ ድምጽ መስጠት (በእንግሊዘኛ) ይፈቀድ እንደሆነ ያረጋግጡ ወይም ቀደም ብሎ ድምጽ ስለሚሰጥባቸው ቀናት እና በእርሶ አካባቢ (በእንግሊዘኛ) ስላለው ደንብ ያረጋግጡ፡፡
በፖስታ ስለመምረጥ እና የቀሪ ድምጽ መስጠት
አንዳንድ ሰቴቶች ምርጫዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ በፖስታ አማካኝነት ያካሂዳሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በአካል ተገኝተው መምረጥ ካልቻሉ ወይም በፖስታ ድምጽ ለመስጠት ከመረጡ የቀሪ ድምጽ መስጫ እንዲጠይቁ ይፈቅዳሉ፡፡ እያንዳንዱ ስቴት የየራሱ መመሪያ አለው፤ ስለሆነም በእርስዎ ስቴት በፖስታ ለመምረጥ የሚፈቀድልዎ መሆኑን ያረጋግጡ (በእንግሊዘኛ)፡፡
በፖስታ አማካኝነት ድምጽ መስጫን ስለመመለስ፦
- በፖስታ፡- በአንዳንድ ስቴቶች እና ግዛቶች ድምጽ መስጫዎች አስቀድሞ ከተከፈለባቸው መመለሻ ፖስታ ጋር አብረው ይመጣሉ፡፡ በሌሎች ደግሞ ኤንቨሎፑን በፖስታ ሳጥን ውስጥ ከመክተትዎ በፊት መላኪያውን መጨመር ያስፈልግዎ ይሆናል፡፡ ከመላክዎ በፊት መመለሻውን ኤንቨሎፕ ሙሉ በሙሉ መሙላትዎን ያረጋግጡ፡፡
- ድምጽ መስጫ ሳጥንን መጠቀም ወይም በአካል መስጠት፦ የምርጫ መስጫዎን ለአካባቢዎ የምርጫ መሥሪያ ቤት ወይም ይፋዊ የድምጽ መስጫ ሳጥን ከመለሱ ማኅተም አያስፈልገዎትም፡፡ ብዙዎች ድምጽ መስጫ ሳጥን ይጠቀማሉ፤ ነገር ግን ያሉበት ቦት እና የመገኘታቸውም ሁኔታ ሊለያይ ይችላል፡፡ በቅርብ የሚገኘው ድምጽ መስጫ ሳጥን በየት እንዳለ ለማወቅ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ይጠይቁ፡፡
ስለድምጽ መስጫዎ ይወቁ
የሚሰጡት ድምጽ በማኅበረሰቡ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በማወቅ መረጃ እንዳገኘ ሰው እንዴት መምረጥ እንዳለብዎ ይማሩ፡፡
በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ናሙና ድምጽ መስጫዎችን በኢንተርኔት ላይ ይለጥፋሉ፡፡ አንዳንዶች እንዲሁ በኢንተርኔት አማካኝነት ወይም በፖስታ ስለ እጩዎች እና ስለ ድምጽ እርምጃዎች መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የስቴትዎን ወይም የአካባቢዎን የምርጫ ዌብሳይት ይፈትሹ፡፡
የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን ይመዝገቡ
ክፍያ የሚከፈለው የምርጫ ሠራተኛ በመሆን ማኅበረሰብዎን ይደግፉ፡፡ የምርጫ ሠራተኛ ተግባራት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ ተመስርቶ የተለያዩ ናቸው፡፡ በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ሥራዎችን የሚሰሩ የምርጫ ሠራተኞች አሏቸው፣ ከሥራዎቹም መካከል፦
- የምርጫ ቦታ ማዘጋጀት
- መራጮችን መቀበል
- የመራጭ ምዝባን ማረጋገጥ
- ድምጽ መስጫን ማሰራጨት
- መራጮች የመምረጫ መሣሪያዎች እንዲጠቀሙ ማገዝ
- የምርጫ አካሄድን ማብራራት
እንደ ምርጫ ሠራተኛ ለጊዜዎ ክፍያ ያገኛሉ፡፡ የክፍያው መጠን በቦታው ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እንዴት የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን እንደሚችሉ በይበልጥ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡