በዚህ ገጽ ላይ የሚገኘው መረጃ ቋሚ አድራሻ ለሌለው ለማንኛውም ሰው ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩ ወይም የነበሩበትን ስፍራ ለቀው ወደ አዲሱ መኖሪያቸው ከመድረሳቸው በፊት ላይ ይሉ ሰዎችበዚህ ስር ይካተታሉ፡፡ ምናልባት ኢንተርኔት ለእርስዎ ያለው ተደራሽነት የተገደበ ከሆነ፤ ምርጫን የሚመለከቱ መልሶች ለማግኘት ወደ አካባቢዎ የምርጫ መሥሪያ ቤት በአካል ሊሄዱ ወይም በስልክ ደውለው ጥያቄዎን ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ የስቴትዎን ወይም የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት በኦንላይን (በእንግሊዘኛ) አድራሻውን እና ስልክ ቁጥሩን ያግኙ ወይም ከአካባቢዎ ቤተ መጽሐፍት ተጨማሪ መረጃ ያግኙ፡፡
ምናልባት የቤት አልባዎች አገልግሎት ሰጪ ከሆኑ፤ United States Interagency Council on Homelessnessሰዎች እንዲመርጡ ለማገዝ ተጨማሪ ግብአቶች አሉት (በእንግሊዘኛ)፡፡
ለመመዝገብ ምን ያስፈልግዎታል
አንዳች ዓይነት መታወቂያ ያስፈልግዎታል
እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት የየራሱ የሆነ የመራጮች መለያ ደንቦች አሉት፡፡ ለመምረጥ ለመመዝገብ መታወቂያ ላያስፈልግዎ ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን በብዙዎቹ ስቴቶች በአካል ለመምረጥ መታወቂያ ማምጣት አለብዎ፡፡ በኦንላይን አማካኝነት የስቴትዎን ልዩ የመታወቂያ መስፈርቶች ምን እንደሆኑ ማረጋገጥ (በእንግሊዘኛ) ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ ለመመዝገብ እና ለመምረጥ ምን ዓይነት መታወቂያ እንደሚያስፈልግዎ ለማወቅ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡
ምናልባት መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ምን ሊከሰት ይችላል?
ምናልባት የማያሽከረክሩ እንኳን ቢሆኑ ከስቴትዎ የሞተር ተሽከርካሪዎች ቢሮ የመታወቂያ ካርድ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ መታወቂያ ካርድ ለማግኘት መክፈል ሊኖርዎ ይችል ይሆናል፤ ነገር ግን የመታወቂያውን ክፍያ ለመክፈል እንዲችሉ ሊያግዙዎ የሚችሉ ድርጅቶች አሉ፡፡ አንዳንድ ስቴቶች በተጨማሪ ለቤት አልባዎች መታወቂያዎችን በነጻ ወይም በቅናሽ ዋጋ ይሰጣሉ፡፡
የፖስታ አድራሻ ያስፈልግዎታል
ስቴትዎ ወሳኝ የምርጫ መረጃዎችን በፖስታ ሊልክልዎ እንዲችል የፖስታ አድራሻዎን መስጠት ይኖርብዎታል፡፡ የፖስታ አድራሻዎ ቋሚ የቤት አድራሻ መሆን የለበትም፡፡ ምናልባት ፖስታ ለማግኘት ቋሚ የቤት አድራሻ ከሌለዎ፤ የፖስታ አደራሻ እንዲሆንዎ ሌላ አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው የፖስታ አድራሻዎች ምሳሌዎች፦
- በአሁኑ ጊዜ በዚያ እንኳን ባይኖሩ በቅረብ ያለ መጠለያ
- በቅረብ የሚገኝ የኃይማኖት ማዕከል
- ጀነራል ዴሊቨሪ (በእንግሊዘኛ) ምናልባት የአካባቢዎ የፖስታ መሥሪያ ቤት የሚያቀርበው ከሆነ
- በሚኖሩበት አቅራቢያ የሚገኝ የፖስታ ቤት ሳጥን
- በቅርብ የሚኖር ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል የቤት አድራሻ
የሚኖሩበትን ወይም የሚተኙበትን ቦታ መግለጫ እንደ ቤት አድራሻ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፤ ይህም ማለት ለምሳሌ ፓርክ ወይም የመንገድ መገናኛዎች ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን መግለጫ እንደ ፖስታ አድራሻ ሊጠቀሙበት አይችሉም።
ምናልባት ከዚህ በሚከተሉት አድራሻዎች የሚኖሩ ከሆነ አሁን የሚኖሩበትን አድራሻ እንደ ሁለቱም ማለትም እንደ ቤት ወይም ፖስታ አድራሻ ይጠቀሙበት፦
- መጠለያ
- ኃይማኖታዊ ማዕከል
- ማናቸውም ሌላ የማኅበረሰብ ቦታ
ምናልባት የትኛውን አድራሻ መጠቀም እንዳለብዎ እርግጠኛ ካልሆኑ፤ ስቴት ወይም የአካባቢ የምርጫ መሥሪያ ቤት (በእንግሊዘኛ) ይጠይቁ፡፡
ምናልባት ለመምረጥ ከተመዘገቡ በኋላ የአድራሻ ለውጥ ካደረጉ
የቤት እና የፖስታ አድራሻዎን ለማዘመን (በእንግሊዘኛ) የአካባቢ የምርጫ መሥሪያ ቤትዎ ጋ መደወል ወይም በአካል መሄድን አይርሱ፡፡ ብዙዎች ስቴቶች በስቴት የምርጫ ድረገጽላይ አድራሻዎን እንዲቀይሩ ይፈቅዳሉ፡፡ ከዚህም ሌላ አድራሻዎ ላይ ለውጥ ለማድረግ የምርጫ መስሪያ ቤትዎ ጋ መደወል ወይም በአካል መሄድ ይችላሉ፡፡ አድራሻዎን ካዘመኑ በኋላ፤ በአዲሱ ቦታዎ መምረጥ ይችላሉ፡፡
በአንዳንድ ስቴቶች በዚያ ለመምረጥ ከመመዝገብዎ በፊት ለተወሰኑ ቀናት መኖር አለብዎ፡፡ የስቴትዎን የነዋሪነት ደንቦች በተመለከተ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ይጠይቁ፡፡
ምናልባት በምዝገባ እና በምርጫ በማድረግ ላይ ተጨማሪ ድጋፍ ካስፈለገዎ
የመራጭ ምዝገባዎን ወይም በፖስታ ለመምረጥ ቅጽ ለመሙላት እገዛ ያግኙ
የስቴትዎ ወይም የአካባቢዎ የምርጫ መሥሪያ ቤት የመራጭ ምዝገባዎን ለመሙላት ወይም በፖስታ ለመምረጥ ጥያቄ እንዲያቀርቡ ሊያግዝዎ ይችላል። በአካባቢ ያለ የቤት አልባዎች መጠለያ ወይም ፕሮግራም በተጨማሪ ሊያግዝዎ ይችል ይሆናል፡፡
ወደ ምርጫ ቦታዎ ለመሄድ መጓጓዣ ያግኙ
በአካባቢ ቡድኖች ወይም በራይድ መጋራት አገልግሎት አማካኝነት ያለ ክፍያ ወደ ምርጫ ቦታዎ ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ ስላሉዎት አማራጮች የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ወይም የአካባቢ መጠለያ ይጠይቁ፡፡
የምዝገባ መሠረታዊ ነገሮች
የምርጫ ምዝገባን በተመለከተ ሌሎች ሊያውቋቸው የሚገቡ መረጃዎች እነዚሁና፡፡
የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን ይወቁ
በብሔራዊ ምርጫ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀን የለም፡፡ በአንዳንድ ስቴቶች የመጨረሻው የምዝገባ ቀን ከምርጫው ቀን ከ30 ቀናት አስቀድሞ ነው፡፡ በሌሎች ስቴቶች ደግሞ በምርጫ ቀን መመዝገብ ይችላሉ፡፡ የምርጫ ቀን የሚለው አገላለጽ ማንኛውንም ምርጫ የሚመለከት ነው (የአካባቢ፣ የስቴት ወይም ብሔራዊ ምርጫ)። በስቴትዎ የመራጭ ምዝገባ የመጨረሻ ቀንን ያግኙ (በእንግሊዘኛ)፡፡
የመራጭ ምዝገባ ካርድዎ
ለመምረጥ ሲመዘገቡ ወይም ምዝገባዎን ሲቀይሩ፤ የመራጭ የምዝገባ ካርድ ይላክልዎታል፡፡ ይህ ካርድ ለመምረጥ መመዝገብዎን እና ዝግጁ መሆንዎን ያረጋግጣል፡፡ ለመምረጥ የመራጭ ምዝገባ ካርድዎን መያዝ አይጠበቅብዎትም፤ ነገር ግን አንዳች ዓይነት ማንነትዎን ለመለየት የሚያስችል መታወቂያ ማቅረብ ይኖርብዎት ይሆናል፡፡ በስቴት ወይም በአካባቢ ምርጫ ድረገጽ (በእንግሊዘኛ) የመራጭ ምዝገባ ካርድ እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ይወቁ፡፡
ምዝገባዎ የዘመነ መሆኑን ያረጋግጡ
በስቴትዎ ድረገጽ በትክክለኛው ሕጋዊ ስምዎ እና አድራሻዎ መመዝገብዎን ያረጋግጡ፡፡ በበርካታ ስቴቶች በተጨማሪ በመጀመሪያ ደረጃ ምርጫዎች እርስዎ በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲመዘገቡ ሊጠይቁ ይችላሉ። የመራጭ ምዝገባ ሁኔታዎን ለማረጋገጥ በስቴትዎ የምርጫ ድረገጽ ላይ ስቴትዎን ወይም ግዛትዎን ይምረጡ፡፡
በመጨረሻዎቹ ሁለት የፌዴራል ምርጫዎች ድምጽ ካልሰጡ ወይም የምርጫ ኃላፊዎች ሊያገኙዎ ሲሞክሩ ካልተገኙ ምዝገባዎ “ንቁ ያልሆነ” ተብሎ ሊያዝ ይላል፡፡ የስቴትዎ ወይም የአካባቢዎ የምርጫ መሥሪያ ቤት ምዝገባዎን ወደ ንቁ ለመቀየር ሊያግዝዎ ወይም ጥያቄ ካለዎ መልስ ሊሰጥዎ ይችላል፡፡
ለመምረጥ ዝግጁ ነዎት?
የምርጫ ዘዴዎች በስቴት እና በግዛት ይለያያሉ፡፡ ለመምረጥ ዝግጁ እንዲሆኑ ዕቅድ ያውጡ፡፡
በአካል ስለመምረጥ
ብዙዎቹ በምርጫ ቀን የሚመርጡ ሰዎች በምርጫው ቦታ በአካል ተገኝተው መምረጥ አለባቸው፡፡ በምርጫ ቦታው ላይ ሲደርሱ፣ የምርጫ ሠራተኞች እርስዎን ለማገዝ ዝግጁ ሆነው ያገኟቸዋል፡፡ በወረቀት ድምጽ መስጫ አማካኝነት የሚፈልጓቸውን በመምረጥ ወይም የኤሌከትሮኒክ መሣሪያ በመጠቀም ድምጽ ይሰጣሉ፡፡
የእርስዎን የምርጫ ቦታ ያግኙ (በእንግሊዘኛ)። የምርጫ ቦታ መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜያት ከአካባቢ አካባቢ የስልጣን ሽፋን መሰረት ይለያያሉ፡፡ ምናልባት ስለምርጫ ቦታዎ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት የስቴት ወይም የአካባቢ የምርጫ መሥሪያ ቤቶችን (በእንግሊዘኛ) ያነጋግሩ፡፡
በፖስታ ስለመምረጥ እና የቀሪ ድምጽ መስጠት
አንዳንድ ሰቴቶች ምርጫዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ በፖስታ አማካኝነት ያካሂዳሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በአካል ተገኝተው መምረጥ ካልቻሉ ወይም በፖስታ ድምጽ ለመስጠት ከመረጡ የቀሪ ድምጽ መስጫ እንዲጠይቁ ይፈቅዳሉ፡፡ እያንዳንዱ ስቴት የየራሱ መመሪያ አለው፤ ስለሆነም በእርስዎ ስቴት በፖስታ ለመምረጥ የሚፈቀድልዎ መሆኑን ያረጋግጡ (በእንግሊዘኛ)፡፡
በፖስታ አማካኝነት ድምጽ መስጫን ስለመመለስ፦
- በፖስታ፡- በአንዳንድ ስቴቶች እና ግዛቶች ድምጽ መስጫዎች አስቀድሞ ከተከፈለባቸው መመለሻ ፖስታ ጋር አብረው ይመጣሉ፡፡ በሌሎች ደግሞ ኤንቨሎፑን በፖስታ ሳጥን ውስጥ ከመክተትዎ በፊት መላኪያውን መጨመር ያስፈልግዎ ይሆናል፡፡ ከመላክዎ በፊት መመለሻውን ኤንቨሎፕ ሙሉ በሙሉ መሙላትዎን ያረጋግጡ፡፡
- ድምጽ መስጫ ሳጥንን መጠቀም ወይም በአካል መስጠት፦ የምርጫ መስጫዎን ለአካባቢዎ የምርጫ መሥሪያ ቤት ወይም ይፋዊ የድምጽ መስጫ ሳጥን ከመለሱ ማኅተም አያስፈልገዎትም፡፡ ብዙዎች ድምጽ መስጫ ሳጥን ይጠቀማሉ፤ ነገር ግን ያሉበት ቦት እና የመገኘታቸውም ሁኔታ ሊለያይ ይችላል፡፡ በቅርብ የሚገኘው ድምጽ መስጫ ሳጥን በየት እንዳለ ለማወቅ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ይጠይቁ፡፡