የምርጫ መመሪያ

ከአሜሪካዊያን እጅግ ጠቃሚ መብቶች መካከል አንዱ የመምረጥ መብት ነው፡፡ ምርጫ ማኅበረሰብዎን ለመቅረጽ እንዲረዳዎ ዕድል ይሰጥዎታል፡፡ 

Vote stickers with American flags.

መቼ እና የት ስለመምረጥ

አብዛኞቹ ስቴቶች እና ግዛቶች የእርስዎን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሉ እንደሁኔታው ምቹ አማራጮችን ይሰጣሉ፡፡ በእርስዎ ስቴት ውስጥ ሊገኙ የሚችሉ አማራጮች እነዚህ ናቸው፡፡

በአካል ስለመምረጥ

ብዙዎቹ በምርጫ ቀን የሚመርጡ ሰዎች በምርጫው ቦታ በአካል ተገኝተው መምረጥ አለባቸው፡፡ በምርጫ ቦታው ላይ ሲደርሱ፣ የምርጫ ሠራተኞች እርስዎን ለማገዝ ዝግጁ ሆነው ያገኟቸዋል፡፡ በወረቀት ድምጽ መስጫ አማካኝነት የሚፈልጓቸውን በመምረጥ ወይም የኤሌከትሮኒክ መሣሪያ በመጠቀም ድምጽ ይሰጣሉ፡፡

የእርስዎን የምርጫ ቦታ ያግኙ (በእንግሊዘኛ)። የምርጫ ቦታ መክፈቻ እና መዝጊያ ጊዜያት ከአካባቢ አካባቢ የስልጣን ሽፋን መሰረት ይለያያሉ፡፡ ምናልባት ስለምርጫ ቦታዎ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት የስቴት ወይም የአካባቢ የምርጫ መሥሪያ ቤቶችን (በእንግሊዘኛ) ያነጋግሩ፡፡

በፖስታ ስለመምረጥ እና የቀሪ ድምጽ መስጠት

አንዳንድ ሰቴቶች ምርጫዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ በፖስታ አማካኝነት ያካሂዳሉ፡፡ ሌሎች ደግሞ በአካል ተገኝተው መምረጥ ካልቻሉ ወይም በፖስታ ድምጽ ለመስጠት ከመረጡ የቀሪ ድምጽ መስጫ እንዲጠይቁ ይፈቅዳሉ፡፡ እያንዳንዱ ስቴት የየራሱ መመሪያ አለው፤ ስለሆነም በእርስዎ ስቴት በፖስታ ለመምረጥ የሚፈቀድልዎ መሆኑን ያረጋግጡ (በእንግሊዘኛ)፡፡ 

በፖስታ አማካኝነት ድምጽ መስጫን ስለመመለስ፦

  • በፖስታ፡- በአንዳንድ ስቴቶች እና ግዛቶች ድምጽ መስጫዎች አስቀድሞ ከተከፈለባቸው መመለሻ ፖስታ ጋር አብረው ይመጣሉ፡፡ በሌሎች ደግሞ ኤንቨሎፑን በፖስታ ሳጥን ውስጥ ከመክተትዎ በፊት መላኪያውን መጨመር ያስፈልግዎ ይሆናል፡፡ ከመላክዎ በፊት መመለሻውን ኤንቨሎፕ ሙሉ በሙሉ መሙላትዎን ያረጋግጡ፡፡
  • ድምጽ መስጫ ሳጥንን መጠቀም ወይም በአካል መስጠት፦ የምርጫ መስጫዎን ለአካባቢዎ የምርጫ መሥሪያ ቤት ወይም ይፋዊ የድምጽ መስጫ ሳጥን ከመለሱ ማኅተም አያስፈልገዎትም፡፡ ብዙዎች ድምጽ መስጫ ሳጥን ይጠቀማሉ፤ ነገር ግን ያሉበት ቦት እና የመገኘታቸውም ሁኔታ ሊለያይ ይችላል፡፡ በቅርብ የሚገኘው ድምጽ መስጫ ሳጥን በየት እንዳለ ለማወቅ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ይጠይቁ፡፡

ስለምርጫ የበለጠ ይወቁ

ስለድምጽ መስጫዎ ይወቁ

የሚሰጡት ድምጽ በማኅበረሰቡ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንደሚያሳድር በማወቅ መረጃ እንዳገኘ ሰው እንዴት መምረጥ እንዳለብዎ ይማሩ፡፡

በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ናሙና ድምጽ መስጫዎችን በኢንተርኔት ላይ ይለጥፋሉ፡፡ አንዳንዶች እንዲሁ በኢንተርኔት አማካኝነት ወይም በፖስታ ስለ እጩዎች እና ስለ ድምጽ እርምጃዎች መረጃ ይሰጣሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የስቴትዎን ወይም የአካባቢዎን የምርጫ ዌብሳይት ይፈትሹ፡፡

የመራጮች መለያ መስፈርቶች

እያንዳንዱ ስቴት እና ግዛት የየራሱን የመራጭ መለያ ደንቦች ያወጣል፡፡ በአብዛኛዎቹ ስቴቶች በአካል ተገኝተው መምረጥ መታወቂያዎን ይዘው መቅረብ፤ በፖስታ አማካኝነት ሲመርጡ ደግሞ የማንነትዎን መረጃ መስጠት አለብዎ፡፡ የስቴትዎን የመራጭ መታዊቂያዎች መስፈርቶችን ያረጋግጡ (በእንግሊዘኛ)፡፡

ምንም እንኳን የማያሽከረክሩ ቢሆንም ከስቴትዎ የሞተር ተሽከርካሪ መሥሪያ ቤት መታወቂያ ማግኘት ይችላሉ፡፡ መታወቂያ ለማግኘት ክፍያ መፈጸም ይኖርብዎታል፤ ነገር ግን ከመታወቂያ ጋር ለተያያዙ ክፍያዎች ምናልባት እገዛ ሊያደርጉልዎ የሚችሉ ድርጅቶች አሉ፡፡

ድምጽ ለመስጠት የመራጭ መለያ ካርድ አያስፈልገዎትም፡፡

የቋንቋ ድጋፍ

ምናልባት እንግሊዝኛ የእርስዎ ዋነኛው ቋንቋዎ ካልሆነ እና በሌላ ቋንቋ መምረጥ ከፈለጉ፤ እገዛ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ በእርስዎ ቋንቋ ምን ዓይነት ድጋፍ እንደሚሰጥ ለማወቅ የአካባቢዎን የምርጫ መሥሪያ ቤት ያነጋግሩ፤ ከእነርሱም መካከል፡ 

  • በእርስዎ ቋንቋ የተዘጋጀ የምርጫ መረጃ እና ማቴሪያሎች (ለምሳሌ ድምጽ መስጫ) 
  • በእርስዎ ቋንቋ ሊያነጋግርዎ የሚችል የምርጫ ሠራተኛ (የአሜሪካን የምልክት ቋንቋ ጨምሮ)
  • በምርጫ ቦታ ለእርስዎ ሊያስተረጉም የሚችል የቤተሰብ አባል ወይም ጓደኛ

የተደራሽነት አቅርቦቶች

ምናልባት የአካል ጉዳተኝነት ካለብዎ፤ ተደራሽ የምርጫ ቁሶች ለምሳሌ ድምጽ መስጫዎች በትልልቅ ህትመት ወይም በድምጽ የማግኘት ህጋዊ መብት አለዎ፡፡ የሚመርጡት በአካል ተገኝተው ከሆነ፤ ተደራሽ የምርጫ መገልገያ አቅርቦቶች እና ተደራሽ ድምጽ መስጫ ቦታ የመገኘት መብት አለዎት፡፡ 

ምናልባት የስቴትዎ የምርጫ ድረገጽ ወይም የድምጽ መስጫው ስፍራ ተደራሽ ካልሆነ፤ የተደራሽነት አገልግሎት አቅርቦቶችን የመጠየቅ አማራጭ መብት አለዎት፡፡ ምናልባት ከዚህ በሚከተሉት ሁኔታዎች የአካባቢ የምርጫ መሥሪያ ቤት ያነጋግሩ፡፦

  • የስቴትዎን የምርጫ ድረገጽ ለማግኘት ከተቸገሩ
  • በድምጽ መስጫው ቦታ የሚያስፈልግዎትን የተደራሽነት አገልግሎት አቅርቦቶችን ለማግኘት ካልቻሉ

በሚመርጡበት ጊዜ በአካል ጉዳተኝነት ምክንያት መድልዖ ደርሶብኛል ብለው ካመኑ ለ Department of Justice ያጋጠመዎትን ሁኔታ ሪፖርት ያድርጉ (በእንግሊዘኛ)፡፡

የአካል ጉዳተኛ ሆነው ሳሉ ስለመምረጥ ይበልጥ ዝርዝር መመሪያ ያግኙ፡፡

ፌዴራል ሕግጋት ለእርስዎን የምርጫ መብት ጥበቃ ያደርጋሉ

ከDepartment of Justice በየመምረጥ መብትዎ መመሪያ (በእንግሊዘኛ) አማካኝነት ስለ መምረጥ መብትዎ ጥበቃ ስለሚያደርጉ የፌዴራል ሕግጋት ይወቁ፡፡ ይህ መምሪያ በተጨማሪ በስፓንሽኛ ቋንቋ ይገኛል፡፡

የመምረጥ መብትዎን በመጠቀም ላይ ሳሉ ከዚህ ከሚከተሉት መካከል ማንኛውም ካገጠመዎ አቤቱታዎን ለDepartment of Justice ያቀርቡ (በእንግሊዘኛ)፡፦

  • ማንኛውም ሰው የመምረጥ መብትዎን ጥያቄ ውስጥ የከተተ እንደሆነ 
  • በሚኖሩት የምርጫ ቁሶች በተወሰነ ቋንቋ እንዲቀርቡ የሚጠየቅ ሆኖ ሳለ እርስዎ ግን እነዚያን ቁሶች ካላገኙ 
  • ምክንያታዊ የተደራሽነት ግልጋሎት አቅርቦቶችን ካላገኙ 

መንግሥት ድምጽዎ እንዴት በትክክል መቆጠሩን እንደሚያረጋግጥ በይበልጥ ይወቁ፡፡

የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን ይመዝገቡ

ክፍያ የሚከፈለው የምርጫ ሠራተኛ በመሆን ማኅበረሰብዎን ይደግፉ፡፡ የምርጫ ሠራተኛ ተግባራት በሚኖሩበት አካባቢ ላይ ተመስርቶ የተለያዩ ናቸው፡፡ በርካታ የምርጫ መሥሪያ ቤቶች ሥራዎችን የሚሰሩ የምርጫ ሠራተኞች አሏቸው፣ ከሥራዎቹም መካከል፦

  • የምርጫ ቦታ ማዘጋጀት 
  • መራጮችን መቀበል 
  • የመራጭ ምዝባን ማረጋገጥ 
  • ድምጽ መስጫን ማሰራጨት  
  • መራጮች የመምረጫ መሣሪያዎች እንዲጠቀሙ ማገዝ 
  • የምርጫ አካሄድን ማብራራት 

እንደ ምርጫ ሠራተኛ ለጊዜዎ ክፍያ ያገኛሉ፡፡ የክፍያው መጠን በቦታው ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ እንዴት የምርጫ ሠራተኛ ለመሆን እንደሚችሉ በይበልጥ ይወቁ (በእንግሊዘኛ)፡፡