የተደራሽነት መግለጫ

በvote.gov ለተደራሽነት ቁርጠኞች ነን። አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ ማንኛውም ሰው የተሟላ እና እኩል የሆነ የድምጽ መስጫ ግብአቶችን ማግኘቱን ማረጋገጥ የእኛ ፖሊሲ ነው። የvote.gov ድረገጽ አካል ጉዳተኞች በድረገጾች ላይ መረጃን እንዲያገኙ ከሚያግዙ መገልገያ መሳሪያዎች ጋር በጥሩ ሁኔታ መስራቱን ለማረጋገጥ በተወሰኑ ቴክኖሎጂዎች ላይ የተመሰረተ ነው። እነዚህ ቴክኖሎጂዎች HTML፣ WAI-ARIA፣ CSS እና JavaScriptን ያካትታሉ። ገፁ በስክሪን ማንበቢያዎች፣ ስክሪን ማጉያዎች፣ የንግግር መለያ ሶፍትዌር እና ሌሎች አጋዥ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም ቀላል መሆኑን ያረጋግጣሉ።

ይዘት

የተደራሽነት መግለጫ

የvote.gov ቡድን ማየት፣ መስማት፣ የኮምፒዩተር ሃርድዌር መጠቀም ለሚቸግራቸው ወይም የግንዛቤ ወይም የመማር ችግር ያለባቸውን ጨምሮ ለሁሉም መራጮች ተደራሽ የሆነ ድረገጽ ለመፍጠር ቁርጠኛ ነው። እኛ በተጨማሪ የመጀመሪያ ቋንቋቸው እንግሊዘኛ ያልሆኑትን ጨምሮ አገልግሎት በሚገባ የማይደርሳቸውን ሰዎች ለማግኘት እንጥራለን። ተደራሽነት ቀጣይነት ያለው ጥረት ነው፤ እና ይዘታችንን ለሚጽፉ፣ ሰነዶቻችንን ለሚያዘጋጁ እና ድረገጻችንን ለሚገነቡ ሰራተኞች መደበኛ ስልጠና በመስጠት ገጻችንን ለማሻሻል እንጥራለን።

ተደራሽነትን እንዴት እንደምንደግፍ እና እንደምንጠብቅ

የሚከተሉትን በማድረግ የvote.gov ተደራሽነትን እናረጋግጣለን፦

  • ለኪቦርድ እና ለስክሪን አንባቢ ተደራሽነት ይዘትን በእጅ በመፈተሽ
  • ይዘቱን ለማደራጀት የፍቺ ክፍል ርዕሶችን በመጠቀም
  • ሁሉንም የድረገጻችን አገናኞች እና መስተጋብራዊ ክፍሎች ያገኙ ዘንድ ሰዎች ኪቦርዱን እንዲጠቀሙ በመፍቀድ
  • "ወደ ዋናው ይዘት ይለፉ" የሚለውን ተግባራዊ እንዲሆን በመጨመር
  • ለስክሪን አንባቢዎች "በአዲስ መስኮት እየተከፈተ" እንደሆነ ለማሳወቅ ወደ ውጫዊ አገናኞች ኮድ በመጨመር
  • ለምስሎች፣ ለአዶዎች እና ለአርማዎች ዝርዝር አማራጭ ጽሑፍ በማቅረብ
  • አውድ እና የተጠቃሚ ተሞክሮ ለማቅረብ ሰዎችን በይዘት ትርጉም ውስጥ በማሳተፍ
  • ተጠቃሚዎች እንደ ምርጫቸው የጽሑፍ መጠን እንዲቀይሩ በመፍቀድ

የእኛ የተደራሽነት ደረጃዎች

ድረ-ገጾቻችንን የSection 508 መስፈርቶች የሚያሟሉ ወይም የሚበልጡ እንዲሆኑ አድርገን እንቀርጻለን፤ እነዚህም የፌዴራል ክፍል 508 ህግን ማክበራችንን የሚያረጋግጡ ቴክኒካዊ መስፈርቶች ናቸው። እንዲሁም ከአለም አቀፍ ድር ኮንሰርቲየም (W3C፣ የድሩ የበላይ አካል) እና የእነሱ የድር ይዘት ተደራሽነት መመሪያዎች (WCAG) 2.1፣ በW3C website ላይ ሊገኝ ይችላል። እኛ የደረጃ AA መመዘኛዎችን እናሟላለን፤ ይህ ማለት ይዘታችን በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ለብዙ ሰዎች ተደራሽ ነው።

አማካሪ እና ፍተሻ

ተደራሽነትን ለመገምገም እና ለማሻሻል በራስ-ሰር እና በማንዋል ፍተሻ ቀጣይነት ያለው ኦዲት ለማድረግ ራሱን የቻለ ባለሙያ አማካሪ ይዘን እንገኛለን።

ተኳኋኝነት

  • Vote.gov Chrome፣ Firefox፣ Edge እና Safariን ጨምሮ ከአብዛኞቹ ዋና የበይነመረብ አሳሾች ጋር ተኳሃኝ ነው።
  • የVote.gov ይዘት በስማርትፎን፣ በታብሌት፣ በላፕቶፕ ወይም በዴስክቶፕ ላይ ሊታይ ይችላል።

የተደራሽነት እገዛ፣ ግብረ መልስ እና መደበኛ ቅሬታዎች

ለጥያቄዎች፣ አስተያየቶች ወይም መደበኛ ስለ vote.gov ተደራሽነት ቅሬታዎች ካለዎት በSection508-vote@gsa.gov ኢሜይል ይላኩልን። በተጨማሪ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ መሙላት ምርጫዎ እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ። ቡድናችን ለጥያቄዎችዎ፣ አስተያየቶችዎ ወይም ስጋቶችዎ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽ ቋንቋ መልስ መስጠት ይችላል።

Touchpoints ID: votegov-accessibility-survey

እኛን ለማግኘት ሲፈልጉ እባክዎን የሚከተሉትን ያካትቱ፦

  • የድር አድራሻ፣ በተጨማሪ URL በመባልም ይታወቃል። የተለመደ URL http://example.gov/index.html or https://www.example.gov/example ሊሆን ይችላል
  • vote.govን ለማግኘት እየተጠቀሙበት ያለው መገልገያ መሳሪያ እና አሳሽ
  • እየተጠቀሙበት ያለው አጋዥ ቴክኖሎጂ፤ ምናልባት ካለ
  • የችግሩ ዝርዝር እና ማንኛውም ተደራሽ ያልሆነ መረጃ

ማስታወሻ፦ ከፌዴራል በዓላት ወይም መስሪያ ቤቱ ካልተዘጋ በስተቀር ከሰኞ እስከ አርብ በምስራቃዊ ሰዓት አቆጣጠር በመደበኛ የስራ ሰዓታት Section508-vote@gsa.govን እንከታተላለን።

ለተጨማሪ የተደራሽነት እገዛ ከላይ ያለውን ቅጽ በእንግሊዝኛ ወይም በስፓኒሽኛ ይሙሉ።

ለጥያቄዎች፣ አስተያየቶች ወይም ስለማንኛውም vote.gov ይዘት ተደራሽነት መደበኛ ቅሬታዎች ወደ Section508-vote@gsa.gov ኢሜይል ይላኩ።

ገጹ በጁላይ 2023 ተገምግሟል እና ዘምኗልም።